Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት
  • Address በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠ/አ ቢሮ ቁጥር 304፡ ትግራይ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251342406712
  • Website
  • Deadline20 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-20 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስር የሚገኙ ትልልቅ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ቀላል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (አውቶሞቢል እና ዳብል ካፕ ፒክአፕ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት መከራየት ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር MKREU-003/2018


የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስር የሚገኙ ትልልቅ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ቀላል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (አውቶሞቢል እና ዳብል ካፕ ፒክአፕ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት መከራየት ይፈልጋል። ዝርዝሩም እንደሚከተለው ይሆናል።

የጨረታው ቁጥር

ሎት

የተሽከርካሪው ዓይነት

ብዛት

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

MKREU-003/2018

ሎት 1

በኤሌክትሪክ የሚሰራ ዳብል ካፕ ፒክአፕ

>8

ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 8:30 ሰዓት

ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 9:00 ሰዓት

ሎት 2

በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶሞቢል

4 (እንደ አስፈላጊነቱ ይጨምራል ይቀንሳል)

ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 8:30 ሰዓት

ግንቦት 12/2018 ከቀኑ 9:00 ሰዓት

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፡ ማስረጃ ያለው መሆን አለበት፤
  2. በጨረታው መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣ መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው እና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  4. አድራሻ፡- መቐለ ከተማ ከፕላኔት ሆቴል ብሎ ዛምራ ኮንስትራክሽን ህንፃ ላይ የሚገኘው የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304፣
  5. ተጫራቾች ለ120 ቀናት እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት “ለመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት” (MEKELLE REGION ELECTRIC UTILITY) ተከፋይ የሆነ የገንዘብ መጠኑ ሎት1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) እንዲሁም ሎት 2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ መሆን ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥሩ MKREU-003/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
  8. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251342406712 መደወል ይችላሉ።


የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Save Tender