የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት በሳውላ ከተማ እና አካባቢው ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ
የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ ጨረታ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸውን መኪናዎች ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት በሳውላ ከተማ እና አካባቢው ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. በትራንስፖርት ሚኒስቴር ወይም በኢት/ከ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ወይም ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይየብታት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO /ሲፒኦ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
5. የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባርቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ በማካተት ኦርጅናል እና ኮፒውን የፋይናሻል እና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተከታታይ ቀን 8፡30 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዥ ፋይንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
7. የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡45 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና መስጫ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለጨረታ ኮሚቴዎች ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
9. መ/ቤቱ የጥገና አገልግሎት ማግኘት የሚፈልገው በሳውላ ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ ነው።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0931561347/0913304979 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ
