Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እና የመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት፡-

1.     የኤሌክትሮኒክስ ግዥ

2.     የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ

3.     የመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ -

1.     በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤

3.     የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው፣

4.     የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤

5.     የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የምችሉ፤

6.     ለመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ደረጃ 2 /ሁለት እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የምችሉ፣

7.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ዩኒት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መግባት አለባቸዉ።

8.     ተጫራቾች የገቡትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፈርማና ማህተም በማሳረፍ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው 16ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል።

9.     ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ክፍል ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታዉን አከፋፈት አያስተጓጉልም፤

11. የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተዉ ከተግለፀላቸዉ ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መዉሰድ ይችላሉ፡፡

12. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0920978389/0926238209 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

 

በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ

Save Tender