አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በዋናው መስሪያ ቤት እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚገኘው ሪከቨሪ የጥበቃ እና የፅዳትና ተላላኪ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለሚገኙ ቅርንጫፎች የፅዳት እና ተላላኪ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
Lion Insurance Company S.C (አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
ቁ07/25/26
የጥበቃ እና ፅዳት አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ
አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በዋናው መስሪያ ቤት እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚገኘው ሪከቨሪ የጥበቃ እና የፅዳትና ተላላኪ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለሚገኙ ቅርንጫፎች የፅዳት እና ተላላኪ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
❖ በመሆኑም ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ በዘርፉ የተመዘገበና ወቅታዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል!
❖ ስራና ሠራተኛን ለማገናኘት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
❖ በተጨማሪም የታደሰ እና በዘርፉ የተመዘገበ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
❖ ግብር መክፈያ መለያ (TIN) ሰርተፊኬት ያለው
❖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ክሊራንስ እና ጨረታ ለመጫረት የሚያችል ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
ስለሆነም የተጠየቀውን አገልግሎት ማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከ ከአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መስሪያ ቤት ከሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሠዓት ድረስ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የመጫረቻ ሰነዱን በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል በማለት አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መስሪያ ቤት (4 ፎቅ) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ጨረታው ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት 4፡30 በኩባንያው ግዥ ኮሚቴ የሚከፈት ይሆናል።
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና አንበሳ ኢንሹራንስ ህንፃ
ስልክ:- 0116-18-70-00/011-6-62 81 35
