ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሪጀክት ነጭ ቦለቄ (Reject white Pea Beans) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
REPI SOAP AND DETERGENT S.C (ረጲ ሣሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሪጀክት ነጭ ቦለቄ (Reject white Pea Beans) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. የ2018 በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ያለው መሆኑ ይኖርበታል፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO መልክ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፤
3. ለጨረታ የወጣዉ ሪጀክት ነጭ ቦለቄ አድራሻ አማራ ክልል ኮንቦልቻ ከተማ
4. ለዚህ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖረተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስክ 10፡00 ሰዓት ብቻ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ክፍለው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
5. ጨረታው እስከ ሚያዚያ 14,2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ሚያዚያ 14,2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00 ሰአት ዝግ ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 9፡00 አቅርቦትና ክምችት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ ሲሞሉ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
ለበለጠ መረጃ
ረጲ ሣሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ
አድራሻ አዲስ አበባ
ጅማ መንገድ ካራ ቆሬ
ሰኘላይ ቼን ክፍል
ስልክ ቁጥር 0913495669 እና 0912161590
