Tender Detail

Tender Details

  • Company ጉምቢ እህል ድርጅት
  • Address , Phone: 0913812486
  • Website
  • Deadline24 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price2000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-24 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

ጉምቢ እህል ድርጅት በአሁኑ ወቅት በእጁ የሚገኘውን የ2017/18 ምርት ዘመን በ2018 የተገዛዉን ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ጉምቢ እህል ድርጅት


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የእህል ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 2/2018

 

ጉምቢ እህል ድርጅት (Dhabbata Gumbii Midhaanii) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ በOSF፣ ተመስርቶ ወደ ስራ የገባ ድርጅት ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብና በማከማቸት፣ ምርቱን ለሚያቀነባብሩ ድርጅቶችና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በማቅረብ የገበያ መረጋጋትን መፍጠር ነው። ድርጅታችን በአሁኑ ወቅት በእጁ የሚገኘውን የ2017/18 ምርት ዘመን በ2018 የተገዛዉን ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የሚሸጠው የምርት ዓይነትና መጠን፦

ስንዴ (Wheat): 110,000 (መቶ አስር ሺህ) ኩንታል በላይ መረከቢያ ቦታ በባሌ ሮቤ ከተማ

በቆሎ (Maize) 10,000 (አስር ሺህ) ኩንታል በላይ መረከቢያ ቦታ ነቀምቴ ከተማ

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦

1.     በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።

3.     ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ምርቱን የሚረከቡበትን የጊዜ ሰሌዳ እና የትራንስፖርት ሁኔታ በግልጽ ማሳወቅ አለባቸው።

5.     ለፋብሪካ እና እሴት ለመጨመር /value add/ ለሚያደርጉ ልዩ አስተያዬት ለማድረግ ይረዳ ዘንድ መረጃ ማቅረብ

6.     መነሻ ዶክመንት በድርጅቱ ዋና ቢሮ 2000 ብር በመክፍል ተመዝግቦ ሰነዱን መዉሰድ፤

7.     የጨረታ አቀራረብ፦ ተጫራቾች የሚገዙትን የምርት ዓይነት፣ መጠን እና የአንድ ኩንታል ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 የስራ ቀናት ድረስ በዋና መስሪያ ቤት ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ፣ ቢፍቱህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መጨረሻ ቀን ከሰዓት 8፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ7ኛ ቀን ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል።

8.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር፦ 0913 812 486

አድራሻ፦ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ፣ ቢፍቱ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው።

ጉምቢ እህል ድርጅት

Save Tender