የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍርድ ባለመብት ሙስጠፋ ሙሐመድ እና የፍርድ ባለዕዳ አዬቱ ኃይሌ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ በፍርድ ባለዕዳ ስም ተመዝግቦ የነበረው፤ ስፋቱ 250 ካ/ሜ በሆነው ቦታ ላይ ያረፈው የመኖሪያ ቤት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ስለወሰነ መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በዚህ ጨረታ ላይ እንድትሳተፉ ፍ/ቤቱ ይጋብዛል።
የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ሙስጠፋ ሙሐመድ እና
የፍርድ ባለዕዳ አዬቱ ኃይሌ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ
በዱከም ክ/ከተማ፣ መልካ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው፤ ስፋቱ 306 ካ.ሜ የሆነ፣ የቀድሞ ባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ካርታ ቁ BMD-11933/B/20/G-02-5436/00 የተሰጠበት ቀን 11/12/2015 ዓም የሆነው በፍርድ ባለዕዳ አዬቱ ኃይሌ ስም ተመዝግቦ የነበረው፤ በአሁኑ ወቅት በካዳስተር ካርታ ቁ: BME-11933B/016፣ ስፋቱ 250 ካ/ሜ በሆነው ቦታ ላይ ያረፈው የመኖሪያ ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 943,810.29 (ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር ከ29/100) ስለሚሸጥ፤ ንብረቱን መግዛት የሚፈልግ ወገን በ30/08/2018 ዓ.ም ከ8፡00 እስከ 10፡00 ድረስ በሚካሄደው ግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ፤ ማንኛውም ተወዳዳሪ 1/4ኛ የጨረታውን መነሻ ዋጋ በሲፒኦ በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም በማስያዝ እንዲገዙ የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋብዟል።
የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
