Tender Detail

Tender Details


ድርጅታችን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሃይሩፍ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 014/18

 

ድርጅታችን የሃይሩፍ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘጡ የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳደረክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው 04/09 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነደ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ገምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

 

ስልክ ቁጥር፡ 011-1-55-52-30

ድረ ገፅ፡ (www.ethbspe.org )

Berhanena selam printing enterprise

አዲስ አበባ

 

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

Save Tender