Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0911-66 49 88
  • Website
  • Deadline30 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-30 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes , Sanitary Ware

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2017 እና 2018 የበጀት አመት ለሰራተኞቹ ማቅረብ የሚገባውን ቱታ፣ ጋዎን፣ ልዩ ልዩ ዓይነት ጫማዎችና የመፀዳጃ ቤት ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር GN-024/2018 እና G-025/2018

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2017 እና 2018 የበጀት አመት ለሰራተኞቹ ማቅረብ የሚገባውን ቱታ፣ ጋዎን፣ ልዩ ልዩ ዓይነት ጫማዎችና የመፀዳጃ ቤት ወረቀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የተመዘገብ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ የታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ከዚህ በፊት በነበሩ ጨረታዎች የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን የሚያቀርቡ በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 በመክፈል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋናው መ/ቤት እቃ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ወይንም የአስተዳደሩ ጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ላሉት 20 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ20ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።

ከላይ የተመለከቱት ሁለቱ የግዥ መለያዎች የተለያዩ ግዥዎች በመሆናቸው ለየብቻ መቅረብ ይገባቸዋል።

የጨረታ ሰነዱ ከሚጠይቀው ሥነ ሥርዓት ውጭ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የጨረታ ፖስታዎች ውድቅ ሊደረጉ ስለሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥሞና እንዲረዱ እናሳስባለን።

መስሪያ ቤታችን ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ እና ሁኔታ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የመረጃ ስልክ ቁጥር 09 11 66 49 88 መደወል ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

Save Tender