Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመ/ኮ/ጉ/ቢሮ /ሆሳዕና/
  • Address ሆሳዕና ከተማ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0939563749
  • Website
  • Deadline20 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-20 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ2018 ዓ.ም ሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመ/ኮ/ጉ/ቢሮ /ሆሳዕና/


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2018

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ2018 ዓ.ም ሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1.     ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 2. ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ 3. ፕሪንተር፣ 4. ካሜራ፣ ትራይፖድ፣ 6. የካሜራ ሚሞሪ 7. ፣ሌንስ 8. የካሜራ ባትሪ፣ 9. የካሜራ ቦርሳ፣ 10. ገመድ አልባ ማይክ፣ 11. ስፒድ ላይት 12. የስፒዲ ላይት ቻርጀር

በዚህም መሰረት በመስኩ የተሰማሩ ድርጅቶች ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀንና ዓ.ም ጀምሮ በቢሯችን ግዢ/ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር3 ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝቶ በመውሰድ መወዳደር የሚቻል መሆኑን እየገለጽን፡-

1.     በዘመኑ የመንግሥት ግብር የተከፈለበትና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው

2.     የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው

3.     ከፌዴራልም ሆነ ከክልል መንግሥት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተሰጠ የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው፣

4.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር ወይም ያለቫት መሆኑን መግለጽ ይገባቸዋል

5.     አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ተጨማሪ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

6.     ተወዳዳሪዎች ተወዳድረው ያሸነፉትን ዕቃ በ specification መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በሲፒኦ፣ ባልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ስም አሠርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች ውል በሚገባው ስምምነት መሰረት አጠናቀው ማስረከብ እንዳለባቸውና በጊዜ ገደብ ውስጥ አጠናቀው ካላስረከቡ በውሉ መሰረት የሚጠየቁ መሆኑ፣

9.     ጨረታው ይፋ ከሆነበት ቀንና ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ዘውትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

10. መሥሪያ ቤቱ የሚያጫርተውን ጨረታ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ብዛቱን እንደ ሁኔታው የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያና የማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ጨረታው ከመከፈቱ 3 ቀናት በፊት በጽሑፍ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጣ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡

12. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንሻልና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ከነ ኮፒው በ11ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡25 ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

13. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

14. ጨረታውን አስመልከቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0939563749 ደውሎ ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመ/ኮ/ጉ/ቢሮ

/ሆሳዕና

Save Tender