በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ማ/ኢ/ስ/ዕ/ፈ/02/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፡-
• ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡-
አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው፤
4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰዉን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፣
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ አምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ዓ.ም ሞዴል በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ሰነድ መያያዝ አለበት፤
8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣
9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም Bid bond /ቢድቦንድ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. የተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለየማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ሰነዱን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃዉን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ አርጅናልና ሁለት ኮፒ በማለት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛዉ ቀን ከቀን 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፡፡
13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251113658288 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የመ/ቤቱ አድራሻ፡- የወልቂጤ መብራት ሀይል አገልግሎት ፊት ለፊት ፈድሉ ህንፃ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
