በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ሴክቴር መ/ቤቶች ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ፕላን ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ሴክቴር መ/ቤቶች ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. በዘርፉ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፤
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፤
4. የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ክሊራንስ ማቀረብ የሚችል፤
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TN NO/ ያለው/ላት፤
6. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ ነች፣
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ በቼክ በመሎ ኮዛ ወረዳ ፈ/ጽ/ቤት ስም አሰርተዉ ከጨረታ ሠነድ ጋር አንድ ላይ ማሰገባት ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር በማያያዝ ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ በሁለት ወጥ ፖስታዎች ለየብቻዉ በማዘጋጀት ዘውትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 9፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ እንደተመለከተው ለሚጫረቱት ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ ያቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በ15ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት ታሽጎ 9፡30 ላይ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
10. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶችን የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
11. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ዕቃ ወይም ንብረት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ ማስረከብ ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን፣ ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል። የተጠቀሱትን መስፈርቶችን እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ማስረጃዎችን ያላቀረበ እንደሆነ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
ማሳሰቢያ
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544
ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
