በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የቀራንዮ ጤና ጣቢያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮ/ቀ/ክ/ከ/ቀ/ጤ/ጣ/ በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት
ሎት 1. የፎቅ ጥገና ዕድሳት
ሎት 2. የፅህፈት ዕቃዎች
በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ሎት1፣ 17,000.00 ሎት2 10,000.00 ማስያዝ የሚችል።
❖ የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
❖ የጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ በሙሉ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት ዕቃ ብቻ ሲሆን አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ በአደራጃችሁ ጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
❖ አንዱ በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
❖ ተጫራቹ ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
❖ የጨረታ ሰነዱን መሸጫ በየሎቱ ዋጋ ብር 300.00 ነው።
❖ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 59 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4. ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
ጤና ጣቢያው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጤና ጣቢያው ለጨረታ አሸናፊው ውል ከመዋዋሉ በፊት 20% ወደ ላይ መጨመር 20% ወደታች መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተወዳዳሪዎች ለአሸነፉት ዕቃ ባስገቡት ናሙና መሠረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
የሚቀርቡትን እቃዎችን በተቋሙ ጥራት ኮሚቴ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፤
አድራሻ
ከጦር ኃይሎች ወደቀራንዮ የሺደበሌ በሚወስደው መንገድ ወረዳ 08 ፅ/ቤት በስተጀርባ ቀ/ጤ/ጣቢያ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፤ 011-383 9040
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የቀራንዮ ጤና ጣቢያ
