የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ
ሎት 1. የጽሕፈት ዕቃዎች 2,000
ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 3,000
ሎት 3. የቋሚ ዕቃዎች 3,000
ሎት 4. መድሀኒቶች እና የህክምና ዕቃዎች የሚወገዱ መዳህኒቶች 20,000
ሎት 5. የህትመት ስራዎች 2,000
ሎት 6. የደንብ ልብስ 4,000
ሎት 7. የጥገና ስራዎች፣ የውሃና መብራት ጥገና 10,000
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች (አቅራቢዎች) በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
1. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ ህጋዊ የሆነ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውንና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ለዚህም የሰነድ ማረጋገጫ ኮፒ እና ዋናውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀረቧቸውን እቃዎች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ቋሚ እና የህክምና ዕቃዎች በተመለከተ በካታሎማ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
3. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለማግኘት የሚችሉት ከተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ተገቢና የተሟላ ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነው።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
5. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡ ህክምና ላይ የምትወዳደሩ አቅራቢዎች የምታቀርቡት መድሃኒትና ሬጀንቶች የአገልግሎት እና የሚወገዱ መዳህኒቶች ዘመናቸው 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የአንድ ሎትዋጋ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበትከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሽግ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 43 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ማስገባት አለባችሁ፡፡
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው የስብሰባ አዳራሽ አራተኛ ፎቅ ቁጥር 44 ይከፈታል፡፡
10. ተቋሙ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ አቅራቢዎች የጨረታውን ሰነድ ዘነበወርቅ ወይም ከአለርት ሆስፒታል 300 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ ቆሼ የሚባል አካባቢ ሲሆን በዚሁ ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ፋይናንስ እና ግዥ ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 43 መጥቶ መግዛት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ከአለርት ሆስፒታል ጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ከአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን 100 ሜትር ገባ ብሎ /ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ 0113698145
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት
