Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABABA HOUSING DEVELOPMENT CORPORATION (የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን)
  • Address ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ሕንፃ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0940284224
  • Websitehttps://aahdc.gov.et/
  • Deadline20 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-21 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Computer Laptop And Accessories

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በሎት 1 የጽዳት የሥራ መደቦች አገልግሎትና አቅርቦት ግዥ እንዲሁም በሎት 2 Desktop computer እና Laptop computer core i7 ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ADDIS ABABA HOUSING DEVELOPMENT CORPORATION (የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ//011/2018

 

በሎት 1 የጽዳት የሥራ መደቦች አገልግሎትና አቅርቦት ግዥ እንዲሁም በሎት 2 Desktop computer እና Laptop computer core i7 ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ያላችሁ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ በድረ -ገፅ ላይ (Online) የተመዘገቡ እንዲሁም ማስረጃውን ኮፒና ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፤ ድርጅቶች ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01፡ ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4ተኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን እያንዳንዱን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በግልጽ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/010/2018 በሎት እና በሎት 2 ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው የሚከፈተው፡-

ሎት 1 ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (የጽዳት አገልግሎትና አቅርቦት)

ሎት 2 ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም (Desktop computer A Laptop computer core i7) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ሕንፃ

ስልክ ቁጥር፡- 0936 99 35 20/ 0911 36 97 83

 

በቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

Save Tender