የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ ማለትም ሎት1 የኤሌከትሪክ እቃዎች፣ ሎት 2 የመካኒካል እቃዎች፣ ሎት3 የኬሚካል እቃዎች፣ ሎት 4 ቧንቧ እና መገጣጠሚያ፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች እና ሎት 6 አላቂ (የጽህፈት መሳሪያ) እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ ማለትም ሎት1 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 2 የመካኒካል እቃዎች፣ ሎት3 የኬሚካል እቃዎች፣ ሎት 4 ቧንቧ እና መገጣጠሚያ፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች እና ሎት 6 አላቂ (የጽህፈት መሳሪያ) እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እገልፃለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችል
4. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 ማገኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት፣ የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ አይነት ለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ 1 ኦሪጂናል እና 1 ኮፒ በአጠቃላይ 2 ሰነዶችን (ኦርጅናል እና ኮፒ) በማለት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከፍት ሆኖ በ22 ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስገቡ እየገለጽን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን፡፡ ነገር ግን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
9. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ 10% ብር በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0920208146 0914613590፣ 0989887862 ደውለው ማገኘት ይችላሉ፡፡
13. የጨረታው ውድድር በእያንዳንዱ ሎት ጥቅል ድምር ነው።
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
