የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ በ2017/2018 የምርት ዘመን ያመረተውን የስንዴ፣ የጎመን ዘር እና ድፍን ምስር ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ በ2017/2018 የምርት ዘመን ያመረተውን የስንዴ፣ የጎመን ዘር እና ድፍን ምስር ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሥራ /በንግድ/ መስኩ በዘመኑ በ2018 ዓ.ም የተገበረ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬትና በተጨማሪም ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ ስለመሆናችሁ በቅርብ ቀን የተሰጠ የድጋፍ ደብድቤ ማቅረብ የምትችሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ሽያጭ ክፍል ቢሮ አርዳይታ ሀሣሣ ሰብልና ተ/ሀ/ል/ማዕከል ቢሮ እና አዲስ አበባ 22 መዞርያ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘው የኮሌጁ ጉዳይ ፈፃሚ ቢሮ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት እና የምርቶቹን ናሙናዎች በትክክል በማየት መጫረት ይችላሉ፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እስከ 30/7/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ 22 መዞርያ አዲስ ሂይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘው የኮሌጁ ጉዳይ ፈፃሚ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመወዳደርያ ፖስታውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ ፈፃሚ ቢሮ ይከፈታል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለስንዴ ምርት የሲፒኦ መጠን ብር 1,026,032.00
2. ጎመን ዘር ምርት የሲፒኦ መጠን ብር 462,240.00
3. ድፍን ምስር ምርት የሲፒአ መጠን ብር 19,155.00
ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለበት፡፡ ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0224760021 ወይም 0949391329
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አርዳይታ
