Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት
  • Address ጎንደር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0582210221
  • Website
  • Deadline26 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-26 00:00:00
  • Categories Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ደንበኛ የሆነው አቶ ምእራፍ ተገኘ አለሙ ለግብርና ሜካናይሽን ፕሮጀክት አገልግሎት ከባንኩ በኪራይ የወሰደውን የእርሻ ትራክተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ክፍያ በገቡት ውል መሰረት ሊፈጽሙ ባለመቻላቸው ምክንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት


የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ደንበኛ የሆነው አቶ ምእራፍ ተገኘ አለሙ ለግብርና ሜካናይሽን ፕሮጀክት አገልግሎት ከባንኩ በኪራይ የወሰደውን የእርሻ ትራክተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ክፍያ በገቡት ውል መሰረት ሊፈጽሙ ባለመቻላቸው ምክንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል።

 

የተከራይ ሙሉ ስም

በጨረታ የሚሸጠው/የሚከራየው ንብረት የሚገኝበት ቦታ

ጨረታው የሚካሄድበት

የሐራጅ ደረጃ

ዓይነት

አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ

ቀን

ሰዓት

ቦታ

አቶ ምእራፍ ተገኘ አለሙ

ማሲ ፈርጉሰ ትራክተር 132 የፈረስ ጉልበት ያለው ብዛት 01

ሰቲት ሁመራ ዞን ሁመራ ከተማ የባንኩ ሁመራ ቅርንጫፍ

14,221,463.69

ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

ከቀኑ 7፡30-9፡30

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት

ዝግ ጨረታ

ማረሻ ናርዲ ባለ 5 (አምስት) ዲስክ ብዛት 01

መከስከሻ ባልዳን ባለ 24 (ሃያ አራት) ዲስክ ብዛት 01

 

ተጫራቾች በቅድሚያ ሊያውቋቸውና ሊያሟላቸው የሚገቡ ጉዳዮች

የሐራጁ መመሪያ-

1.     ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/5 (አንድ አምስተኛ) ጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በተዘጋጀና በባንክ በተረጋጋጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2.     ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ (ካሸ) ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ የተያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡

3.     ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒአ ወዲያውኑ ይመለሰላቸዋል፡፡

4.     የጨረታው አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ክፍያዎች በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት።

5.     የጨረታው አሸናፊ ባሸነፈው ዋጋ ላይ 15% /VAT/ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

6.     አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሸኑን ጠቅላላ ዋጋ 20 % በቅድሚያ በመክፈል በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟለት የማሸነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡

7.     ንብረቶችን ከጨረታ በፊት ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከባንኩ ጋር ፐሮግራም መያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዝዙበትን ዋጋ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡

8.     ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.     ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582210221/ 0582110184 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት

Save Tender