የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
ለሁለተኛ ዙር የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ከላይ መግለጽ እንደተሞከረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላችው ቫት ተመዝጋቢ ዓመታዊ የስራ ግብር የከፈሉ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ (በፋ/ኢ/ሚኒስቴር / በክልሉ ገቢዎች ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘረውን የእያንዳንዱን ዋጋ ሞልተው፣ ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ፋይናንሻል ኦርጀናል አንድ ፋይናንሻል ኮፒ አንድ እና ቴክኒካል ኦርጅናል አንድ ቴክኒካል ኮፒ አንድ ለብቻ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮን/ባለስልጣን ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመምጣት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ በ400 /በአራት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት /CPO/ ኤሌክትሮኒክስ 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክሜንት ጋር አንድ ላይ አሽጋችሁ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ወዲያውኑ ተጫራች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 6፡00 ታሽጎ 8፡00 ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች በተወዳደሩበት የዕቃ አይነት የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሳቸው መ/ቤት በመምጣት በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ጋራንቲ በማስያዝ ከቢሮው ጋር ውል መግባት አለባቸው።
6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት ዕቃውን በራሱ ማጓጓዣ ቢሮ ድረስ በማቅረብ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይፈራረም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበርያ ያስገባው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ስትሞሉ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት አልያ ውድቅ ይደረጋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነዱ መረዳት ይቻላል፡፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-74-74-93/09-16-03-50-70/09-04-82-92-69
አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቡታጅራ ከተማ ችግኝ ጣቢያ አጠገብ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
