Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)
  • Address ከጐላጐል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር (708): አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011- 667-23-36
  • Websitehttps://dvlca.gov.et/
  • Deadline13 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-13 00:00:00
  • Categories Printed Advertising Materials , Stationery Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

አሽተሽፍቁባ /መግዳ/2018/003

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ሎት 1 የመንጃ ፍቃድ ካርድ ፕሪንተር ሪቫን፣ ላምኔሽንና መንጃ ፍቃድ ካርድ

✔ ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ከሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ ፡፡

✔ ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

✔ የጨረታ ሰነዱን ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት መክሊት ህንፃ 8ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 804 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ገዝታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

✔ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ለሎት ለእያንዳንዳቸው የ500,000 ብር (አምስት መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

✔ ባለስልጣን መስሪያቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

✔ አድራሻ፡- ከጐላጐል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር (708)፤ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-667-23-36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

Save Tender