የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮምባይን ዴስክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 06/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮምባይን ዴስክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
2. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከቢሮአችን ቢሮ ቁጥር 101 በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነዱን በሶፍት ኮፒ ፣ በፍላሽ ወይም በኢሜል መውሰድ ይችላሉ፣
4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አግልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤
5. ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣
6. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ 7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣
7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ድልድል መሰረት እቃውን በየትምህርት ቤቱ በማቅረብ ገቢ ማድረግ አለበት፣
9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
በስልክ ቁጥር 011 122 64 56
አድራሻ:- 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
