Tender Detail

Tender Details

  • Company መስቀል ፍላወር ሆቴል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address , Phone: 0114670126
  • Website
  • Deadline30 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-30 00:00:00
  • Categories Rent

በመስቀል ፍላወር ሆቴል የሚገኘውን 250 ካሬ ሜትር ቦታ ለሱቅ በመነሻ ዋጋ በካሬ 3,000.00(ሶስት ሺ) ብር ለንግድ ስራ አገልግሎት የሚከራዩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል።

መስቀል ፍላወር ሆቴል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በመስቀል ፍላወር ሆቴል የሚገኘውን 250 ካሬ ሜትር ቦታ ለሱቅ በመነሻ ዋጋ በካሬ 3,000.00(ሶስት ሺ) ብር ለንግድ ስራ አገልግሎት የሚከራዩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

1.       ተጫራቾች አሸናፊው እንደተለየ የሚመለስ 5,000.00 (አምስት ሺ ብር) ጨረታ መክፈቻ እለት ለተቋሙ ገንዘብ ያዥ በካሽ ማስያዝ አለባቸው።

2.       ተጫራቾች ለጨረታው የሚቀርበውን ሱቅ ቦታው ድረስ በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ።

3.       ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ፕሮፖዛል በታሸገ ፖስታ ከሰኞ 14/7/2018 እስከ ቅዳሜ 19/7/2018 ድረስ ሆቴሉ እሪሴፕሽን ጋር ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 12፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።

4.       ጨረታው የሚከፈተው ሰኞ 21/7/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈ ታል።

5.       አሸናፊው በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ በእለቱ ከፍሎ ሱቁን በእለቱ ውል ገብቶ ይረከባል።

6.       አሸናፊው ያሸነፈበትን ገንዘብ በእለት ከፍሎ ሱቁን ካልተረከበ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

7.       ሆቴሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.       የጨረታ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) የማይመለስ በመግዛት ጨረታውን ማስገባት ይችላል።

9.       ተከራይ ሆቴሉ የሚያቀርበውን ምንም አይነት አገልግሎት የምግብ እና የመጠጥ አይነቶች ማቅረብም ሆነ መሸጥ አይችልም።

አድራሻ፡- መስቀል ፍላወር ሆቴል አደባባዩ ፊት ለፌት

ስልክ ቁጥር፡-011 467 0126 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

መስቀል ፍላወር ሆቴል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

 

Save Tender