Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት
  • Address ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline14 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-14 00:00:00
  • Categories Building Materials , Construction Works

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 01,02,07,08 እና 10 ለሚያሰራቸው የግንባታ ሥራዎች ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት


 

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 10/2018

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 01,02,07,08 እና 10 ለሚያሰራቸው የግንባታ ሥራዎች ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራወን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

 

ሎት

የፕሮጀክት ስም

ወረዳ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

 

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

አድራሻ

1

ስፖርት ሜዳ ህዳሴ 2 ደረጃ ት/ቤት

02

 

 

 

 

2%

ደረጃ 6 ተቋራጭ ብቻ

 

 

 

 

90 ቀን

 

 

 

ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ

2

ሰብ ቤዝ ሥራ እና ድሬኔጅ ድጋሚ ብሎክ 42

02

ደረጃ 7 እና 8 ተቋራጭ ብቻ

3

ፖሊስ ሴንተር

02

ደረጃ 6 ተቋራጭ ብቻ

4

ሰብ ቤዝ ሥራ ድሬኔጅ ሥራ ብሎክ 19

07

ደረጃ 7 እና 8 ተቋራጭ ብቻ

5

ሰብ ቤዝ ሥራ ድሬኔጀ ሥራ ብሎክ 19 እና ቀጠና 6 /ዋቆ ጉቱ ጀርባ

07

ደረጃ 7 እና 8 ተቋራጭ ብቻ

6

ሰብ ቤዝ ሥራ ድሬኔጅ ሥራ ብሎክ

08

ደረጃ 7 እና 8 ተቋራጭ ብቻ

7

የመንገድ መብራት እቃዎች ግዢ

10

ሕጋዊ ፍቃድ ያለው

8

ሰብ ቤዝ ሥራ ብሎክ 05 እና 17

11

ደረጃ 7 እና 8 ተቋራጭ ብቻ

9

ፖሊስ ሴንተር

01

ደረጃ 6 ተቋራጭ ብቻ

 

1.     ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የ2018 ዓ.ም የከፈሉ፤ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2.     ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፤ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል። በተጨማሪም የታሸገውን 2 ፖስታ የፋይናንሻል እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፤ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)።

3.     ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት (work Days) ቅዳሜን ጨምሮ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፌ/ማ/ጽ/ቤት መሰረት ልማት በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን (work Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፌ/ማ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 16ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

4.     ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጣነ (unbalanced rate) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል።

5.     ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።

6.     በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

7.     እጃቸው ላይ ምንም አይነት ስራ እንደሌላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ስራም ካላቸው 75% መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ። ጨረታ መሳተፍ የሚቻለው በአንድ ሎት ብቻ ነው።

8.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት

Save Tender