Tender Detail

Tender Details

  • Company ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ
  • Address በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-81-63-85
  • Website
  • Deadline03 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price250.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-03 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ሎት1፡- ሰብል ሽያጭ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ባቄላና ማሽላ

ከላይ በሎት 1 /አንድ/ የተዘረዘሩትን ምርቶች በሀገር ውስጥ ገበያ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች በወጣው ማስታወቂያ መሰረት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽ በጨረታው ለመሳተፍ፣

1.     ከላይ በተዘረዘሩት የንግድ ዘርፎች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት/፣

2.     የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣

3.     የንግድ መለያ ቁጥር /TIN/ ኮፒ፣

4.     የቫት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

5.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

6.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ-ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

7.     ለመግዛት የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ የያዘ ጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ መግዛት ይቻላል።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በዩኒዬኑ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠባሴ ቅርንጫፍ 1000602970713 በመክፈል በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሠልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ.የተ/ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበትና ለሚሞሉት ዋጋ 2% ሲፒኦ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በደ/ብርሃን እና አዲስ አበባ ባሉ ባንኮች በዩኒየኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዶክመንት ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ተለያይቶ በአንድ ፖስታ ታሽጎ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ.የተ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ሲሆን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል።

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሠልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

12. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ.የተ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 09 27 04 14 60 በመደወል ማግኘት ይቻላሉ።

 

ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ

Save Tender