የጉራፈርዳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሞተር ሳይክል እና የቢሮ ፈርኒቸር በ2018 በጀት ዓመት በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉራፈርዳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሞተር ሳይክል እና የቢሮ ፈርኒቸር በ2018 በጀት ዓመት በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት አመቱ የሚያገለግል የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ደረጃ 5GC/B.C እና ከዛ በላይ የሆነ ለትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ
3. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በዝርዝር ከታች በሎት በቀረበዉ መሰረት
• ሎት 1 ለትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ
• ሎት 2 ለኤሌክትሮኒክስ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
• ሎት 3. የቢሮ ፈርኒቸር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
• ሎት 4. ለሞተር ሳይክል 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሁሉም ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
1. ከሎት 2 እስከ ሎት 4 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ኬዝቲም ቢሮ ቁጥር 07 ለትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ለግንባታ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ለሌሎች የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን
2. የሎት 1 /አንድ/ ለትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ ይህ ጨረታ በድጋሚ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒ የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በማሸግ መወዳደር ይጠበቅባችዋል።
4. ከሎት 2 እስከ ሎት 4 የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዛዉ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
5. ሎት 1 ለትምህርት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዛዉ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ በጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ ጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር +251-910151128
ስልክ ቁጥር +251-917771604
በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
