በከሳሽ ወ/ሮ ቤቴል ክንፉ እና በተከሳሽ አቶ ክፍሌ እሸቱ መካከል ያለውን የፍርድ አፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ፤ በፊንፊኔ (አዲስ አበባ) ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘው በተከሳሽ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በዚህ ጨረታ ተወዳድራችሁ እንድትገዙ የጨለለቃ ከተማ ወረዳ መደበኛ ፍርድ ቤት አዟል፡፡
በቢሾፍቱ ከተማ ከ/ፍ/ቤት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ መደበኛ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በከሳሽ፡- ወ/ሮ ቤቴል ክንፉ እና በተከሳሽ፡- አቶ ክፍሌ እሸቱ መካከል ያለውን የፍርድ አፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ፤ በፊንፊኔ (አዲስ አበባ) ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘው፣ የቤት ቁጥር 217፣ የቦታው ስፋት 550 ካሬ ሜትር፤ ልዩ መለያ ቁጥሩ AA000040101638 የሆነውና በተከሳሽ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት፣ የጨረታ መነሻ ግምት ዋጋው ብር 2,713,544.74 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ አርባ አራት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም) ሆኖ ይህ ንብረት በጨረታ ስለሚሸጥ፣ በዚህ ጨረታ ተወዳድረው መግዛት የሚፈልጉ ሰዎች የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ (25%) በCPO በማስያዝ እንዲወዳደሩ። ይህ ጨረታ የሚካሄድበት ቀን 20/08/2018 ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 7:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ተገኝተው ተወዳድረው እንዲገዙ የጨለለቃ ከተማ ወረዳ መደበኛ ፍርድ ቤት አዟል።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የገዛበትን ሙሉ ዋጋ መክፈል ይኖርበታል፡፡
በቢሾፍቱ ከተማ ከ/ፍ/ቤት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ መደበኛ ፍ/ቤት
