Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የእርሻ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት


ግልፅ የጨረታማስታመቂያ

የጨረታ ቁጥር ARARI 04 / 07/2018

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የእርሻ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1.       በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2.       የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤

3.       የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4.       ተጫራቾች በጨረታለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤

5.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 119 በግንባር በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

6.       የሚገዙት ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ተያይዟል፤

7.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 120,000.00/አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በCPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፤

8.       ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ 16ኛው ቀን የሚውለው በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

9.       ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ባለሙያዎች ከፍል ቢሮ ቁጥር 120 በ16ኛው ቀን ጠዋት በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ላይ ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ላይ ይከፈታል፤

10.   ተጫራቾች በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤

11.   መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12.   ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 6077 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 5074 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ባህርዳር

Save Tender