በጨለለቃ ክ/ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የቤተሰብና ህፃናት ችሎት ቡድን የመኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል
በጨለለቃ ክ/ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የቤተሰብና ህፃናት ችሎት ቡድን
የጨረታ ማስታወቂያ
በከሳሽ፡- ወ/ሮ ቤቴል ክንፉ እና በተከሳሽ፡- አቶ ክፍሌ እሸቱ መካከል ያለውን የፍርድ አፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ከተማ አዝና ኤረር ውስጥ የሚገኝ፣ የቤት ቁጥር 2437፤ የቦታው ስፋት 210 ካሬ ሜትር፣ የካርታ ቁጥር 44/66/2/37 የሆነውና በተከሳሽ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት፤ የጨረታ መነሻ ግምት ዋጋው ብር 2,290,615.52 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ስድስት መቶ አስራ አምስት ከሃምሳ ሁለት ሳንቲም) ሆኖ ይህ ንብረት በጨረታ ስለሚሸጥ፤ በዚህ ጨረታ ተወዳድረው መግዛት የሚፈልጉ ሰዎች የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ (25%) በCPO በማስያዝ እንዲወዳደሩ። ይህ ጨረታ የሚካሄድበት ቀን 21/08/2018 ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ተገኝተው ተወዳድረው እንዲገዙ የጨለለቃ ከተማ ወረዳ መደበኛ ፍርድ ቤት አዟል።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የገዛበትን ሙሉ ዋጋ መክፈል ይኖርበታል።
በጨለለቃ ክ/ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የቤተሰብና ህፃናት ችሎት ቡድን
