ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር በሚቼል ኮት ግቢ ውስጥ ያለውን የኩባንያችን ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ብረታ ብረት (Metal Scrap) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ በኪሎግራም ለመሸጥ ይፈልጋል
ያገለገሉ ብረታ ብረቶች (Metal Scrap)
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን በሚቼል ኮት ግቢ ውስጥ ያለውን የኩባንያችን ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ብረታ ብረት (Metal Scrap) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ በኪሎግራም ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር ) ለድርጅታችን ሂሳብ ክፍል በማስገባት ያስገቡበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የዘመኑ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ላለው ድርጅቶች ባሉበት ለመሸጥ ስለሚፈልግ ተጫራቾች የምትገዙበትን ያገለገሉ ብረታ ብረት (Metal Scrap) እና ካስት አይረን (Cast lron) ዋጋ በመለየት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በማስያዝ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋሲሊቲና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ንብረቶችን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 – 6፡00 ከሰአት ከ 7፡30 - 11:00 ሰአት በድርጅቱ ሣሪስ 106 ቅርንጫፍ ወይም በፎርድ ተሽከርካሪ የጥገና ማዕከል በአካል ተገኝተው ጨረታ የገዙበትን ሰነድ ለጥበቃ በማሳየት ማመልከት ይችላሉ።
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በሚኖረው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት በሠራተኞች ክበብ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
– የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በራሳቸው ማንሻ ማሸን እና መኪና በአንድ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ የተ.ዕ.ታ ጨምሮ በመክፈል እቃዎችን የማያነሱ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ወደ ድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
– በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው እቃዎቹን የማያነሱ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪው የተያዘው ገንዘብ ወደ ድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
– የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙት CPO ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
– ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0114 421 133 የውስጥ መስመር 212 ወይም 223 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ደብረ ዘይት መንገድ (ሣሪስ አካባቢ)
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1116 አዲስ አበባ
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር
