የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ ጉዶበረት ቀበሌ ቶራ መስክ አካባቢ ደን ሳይት እና አባሞቴ ቀበሌ እምቧጭ ጉር አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው
Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር DWP/Pu-03/74/18 ቀን 09/07/2017
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ ጉዶበረት ቀበሌ ቶራ መስክ አካባቢ ደን ሳይት እና አባሞቴ ቀበሌ እምቧጭ ጉር አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን ሎት 1 ጉዶበረት ቀበሌ ቶራ መስክ አካባቢ ደን ሳይት ለ150 ሰዓት እና ሎት 2 አባሞቴ ቀበሌ እምቧጭ ጉር አካባቢ ደን ሳይት ለ100 ሰዓት አጠቃላይ ለ250 በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-
1. በዘርፉ የተሰማራና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1. ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
6. አሸናፊው ድርጅት ማሽኑን በራሱ ወጪ ስራው የሚሰራበት ጫካ ድረስ የማድረስና ስራውን ሲጨርስ የመመለስ ግዴታ አለበት፣ እንዲሁም የራሱ ኦፕሬተር ሊኖረው ይገባል። የኦፕሬተር ሰርቪስ ተጫራቹ ማቅረብ አለበት፤
7. የአንዱ ሳይት ሥራ ሲጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ሳይት ማሽኑን የማዘዋወር ኃላፊነት የአከራዩ ድርጅት ኃላፊነት ነው።
8. አሸናፊ ተጫራች በስራ ቦታ ላይ ከነዳጅ ወጪ በስተቀር የኤክስካቫተሩን የዘይት፣ ቅባት፣ ግሪስ፣ ሰርቪስ፣ ቀላልና ከባድ ጥገናዎች፣ የጎማ ጥገናና ግዢ፣ የሹፌር ደመወዝ እና አበል እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ።
9. ማሽኑ በስራ ላይ እያለ ቢበላሽ አሸናፊው ተጫራች በራሱ ወጪ የተበላሸውን የማስተካከል ስራ የሚሰራ ሲሆን በቀላሉ ማስተካከል የማይችል ከሆነ በራሱ ወጪ አንስቶ በምትኩ ሌላ ማሽን የማስገባት ግዴታ አለበት።
10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
11. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
13. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
14. የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ላይ ወይም እሁድ ከዋለ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
15. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል።
16. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሁለቱም ሎቶች በአንድ ላይ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ።
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
