ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን ፕራይም ቦቲ (Asphalt Distributor) በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ኀብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
የጨረታ ማስታወቂያ ክፍል አንድ
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን ፕራይም ቦቲ (Asphalt Distributor) በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የማሽኑ አይነት
|
የማሽኑ አቅም
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
የማቅረቢያ ቦታ
|
ምርመራ
|
|
1
|
ፕራይም ቦቲ (Asphalt Distributor)
|
260 HP
|
በቁጥር
|
02
|
አዲስ አበባ
|
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT) ያላቸው መሆን አለበት።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒ. ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል የባንክ ጋራንቲ የተ.እ. ታክስን ጨምሮ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በኮርፖሬሽናችን ስም ማለትም “ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (Hibir Construction Corporation" ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለሚታሰብ ለ9ዐ (ዘጠና) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
3. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለጸው የፕራይም ቦቲ (Asphalt Distributor) ቴክኒካል ኦርጅናል (ዋና) እና ኮፒ (ቅጅ) በማለት ለየብቻ እና የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን የፋይናንሻል ፖስታ ኮፒ (ቅጅ) እና ኦርጅናል (ዋና) በማለት በተለያየ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በፖስታ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ።
6. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን የእቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ እና የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ዋና መ/ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:30 የሚከፈት ሲሆን 2ዐኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-3576 መደወል ይችላሉ።
ኀብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
