Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116200679
  • Website
  • Deadline05 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-05 00:00:00
  • Categories Electronics Materials , Construction Works , Office Equipment

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማኅበረሰብ ፖንድ እና የእጅ ጉድጓድ በደረጃ 8 እና በላይ በWC/GC ዘርፍ ፣ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያየ የቢሮ እቃዎች ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት፣ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማኅበረሰብ ፖንድ እና የእጅ ጉድጓድ በደረጃ 8 እና በላይ በWC/GC ዘርፍ ፣ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያየ የቢሮ እቃዎች ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት፣ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

➢  በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/፤

➢  በዘርፉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት/፤

➢  በሎት 1 እና 2 ላይ የሚወዳደሩ ከሆነ በዘመኑ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፤

➢  ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

➢  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ መሂ-1/፡- ማስያዝ አለባቸው።

 

ሎት

 

የጨረታው ዓይነት

 

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ

 

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

 

1

 

የማህበረሰብ ፖንድ በአባያ ቀበሌ

 

100

 

15000

 

2

 

የእጅ ጉድጓድ በአባያ ቀበሌ

 

100

 

6000

 

3

 

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

 

100

 

10000

 

4

 

የቢሮ አቃዎች ፈርኒቸር

 

100

 

4000

 

5

 

የተለያዩ የውሃ እቃዎች

 

100

 

8000

 

6

 

የግንባታ እቃዎች

 

100

 

2000

 

 

ሎት 1 ላይ የሚወዳደሩት የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ከአደራጃቸው አካል በደብዳቤ ዋስትና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

➢  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር በመክፈል ከሲ/ዋዩ ወ/ገን/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 መግባት ይሻላሉ።

➢  ሎት 1 እና 2 የተገለፀው ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች በገንም ባይንም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።

➢  ከሎት 1 እና 2 በስተቀር ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገጥም ባያገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።

➢  ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናሉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት በመፃፍ ሲያ/ዋ/ወ/ ገን/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው አስገሚዘጋበት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።

➢  አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በየፑሉ በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ገቢ ያደርጋል።

➢  አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ  ደረሰኝ /መሂ -1/ በማስያዝ ውል።

➢  ሎት 3 ፤ 4 እና 6 ዝርዘር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።

➢  መ/ቤቱ በግዥው ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።

➢  የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው።

➢  መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

➢  ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ሰ 011 620 0679 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

 

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር ያሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender