የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮ ስራ ክፍሎች መጋረጃና ለመሰብሰቢያ: አዳራሽ መጋረጃ፤ የወለል ምንጣፍና የሳውንድ ሲስተም ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮ ስራ ክፍሎች መጋረጃና ለመሰብሰቢያ: አዳራሽ መጋረጃ፤ የወለል ምንጣፍና የሳውንድ ሲስተም ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1፦ መጋረጃና የወለል ምንጣፍ
ሎት 2፦ሳውንድ ሲስተም
በዚሁ መሰረት መጫረት የሚችሉት ፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ታክስ ክሊራንስ፤ የቲን ተመዝጋና የቫት ተመዝጋ የሆኑ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ10/ አስር/ ተከታታይ ቀናት ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀ ዝርዝር መግለጫዎች የያዘ ሠነድ (specification) በመግዛት መጫረት ይችላሉ።
3. ጨረታው 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ10፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም በባንክ በተረጋገጠ CPO በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
5. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞለቶ የጨረታ ማስከበሪያ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ(ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ(ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 6፡00 እስከ 8:00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ/ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
7. ጨረታው ለ3 ወራት/90 ቀናት/ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ግ/ክ/ን/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ሕንፃ 04 ክፍል 27 ማግኘት ይቻላል።
9. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
10. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 046 212 6783
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
