Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  • Address ባሕር ዳር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0582180014
  • Website
  • Deadline03 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-03 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመታዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት /የጭነት መኪና/ ትራንስፖርት አገልግሎት በአገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመታዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት /የጭነት መኪና/ ትራንስፖርት አገልግሎት በአገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1.     ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

5.     ስለ አመታዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት /የጭነት መኪና/ ትራንስፖርት አገልግሎት አይነትና ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.አ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፈ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት።

9.     በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፤

10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

11. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በአል እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።

 

የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባህር ዳር

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0582180014/ 0582181103 ይደውሉ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

Save Tender