አልማኮን ሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለኩባንያው አገልግሎት የሚውል ኤክስካቫተር ክእነ ጃካሀመሩ (Chain Excavator with jackhammer) አቅራቢዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የማሽነሪ ግዥ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
አልማኮን ሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለኩባንያው አገልግሎት የሚውል ኤክስካቫተር ክእነ ጃካሀመሩ (Chain Excavator with jackhammer) አቅራቢዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. የማሽነሪ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
4. ተጫራቾች ባሕርዳር በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ወይም አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አካባቢ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን አማራ ልማት ማህበር (አልማ) ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ (unconditional Bank Guarantee) በአልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን ባህርዳር ቀበሌ 07 አማራ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት በሚገኘው የአልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሎጅስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ 6፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
8. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ7ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 07 በኩባንያው ዋናው ቢሮ የሎጅስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም 7ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይክፈታል።
9. የጨረታ አሸናፊ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማሽነሪውን በስፔስፊኬሽኑ መሰረት አሟልቶ አዲስ አበባ ከተማ ግዥ ፈፃሚው ከሚፈልግበት ቦታ ድረስ አጓጉዞ ለግዥ ፈጻሚው (አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግል ማህበር) ያስረክባል።
10. ኩባንያው በማንኛውም ጊዜ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 14 34 00 31/ 09 12 34 34 19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አልማኮን ህንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃ/የተ/የግል ማህበር
