ማህበራችን ፍቅር ለአንድነት የጋራ መኖሪያቤቶች ህ/ሥ/ማህበር ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ክልል ልዩ ቦታው አብነት ክሊኒክ አካባቢ ለሚገኝ ኮንድሚኒየም ከታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች ለማሠራት ይፈልጋል።
ፍቅር ለአንድነት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ህ/ሥራ ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ማህበራችን ፍቅር ለአንድነት የጋራ መኖሪያቤቶች ህ/ሥ/ማህበር ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ክልል ልዩ ቦታው አብነት ክሊኒክ አካባቢ ለሚገኝ ኮንድሚኒየም ከታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች ለማሠራት እንፈልጋለን፡፡
1ኛ የእግረኛ መንገድ ቴራዞ
2ኛ ከርቭ ሰቶን
3ኛ የማኖል ክዳን
4ኛ ግማሽ በሲሚንቶ የተሰራ ትቦ ዝርጋታ እና ሌሎችንም ሥራዎች በሞያው የተሰማራ ከደረጃ ሰባት ጀምሮ የማህበሩ ቢሮ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የሚችል ሲሆን ለጨረታው ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በጥሬው ወይንም በሲፒዮ በማሰያዝ መወዳደር የሚቻል ሲሆን ጨረታው ከ7/7/2018 ዓ/ም እስከ 15/7/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማህበሩ ቢሮ በፖስታ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማህበሩ ሥራውን ለማሠራት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፍቅር ለአንድነት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ህ/ሥራ ማህበር
