በፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማሰ/ተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትከልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ስጋ፣ የተለያዩ ስፖርት ትጥቆች፣ ቶርሽን ጫማ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ሸራ ጫማ ግዥ በማስፈለጉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በቀድሞ ስሙ በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ
የጨረታ ማስታወቂያ
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማሰ/ተቋሙአገልግሎት የሚውሉ
1ኛ የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትከልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ስጋ
2ኛ. የተለያዩ ስፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ ፣ብርድ ልብስ ፣ አንሶላ እና ሸራ ጫማ ግዥ በማስፈለጉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍየምትፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው የአገር ውስጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገንዘብ ሚ/ር የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬትና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ መመሪያና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ የሆነውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከአ/አበባ በደብረብርሃን መስመር 63 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፖሊስ ማሠ/ተቋም ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት የምትችሉ ሲሆን፦
|
|
የእቃው ዓይነት
|
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
|
|
|
የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ስጋ ግዥ
|
መጋቢት 17/07/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል
|
|
|
የተለያዩ ስፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ ፤ብርድልብስ አንሶላ እና ሽራ ጫማ ግዥ
|
መጋቢት 18/07/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል
|
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ ብር 10,000.00/አስር ሺህ/ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ በባንክ ተረጋግጦ በሚሰጥ (CPO) በማሠራት የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታ ውስጥ በማስገባትና በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡ የሚቀርበው ጨረታ ሠነድ በአማርኛመሆኑን እየገለፅን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፤ 0116720000 ፤ 0920169144
0941232737 እና 0913379489 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በቀድሞ ስሙ በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ
