በ/ደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሽኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሸኮ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙት የተለያዩ ቀበሌዎች የመንገድ ከፈታ፣ የቦይ ስራ የሪዎርክ ስራ ለመስራት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ ማሽኖች መከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በ/ደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሽኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሸኮ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙት የተለያዩ ቀበሌዎች የመንገድ ከፈታ፣ የቦይ ስራ የሪዎርክ ስራ ለመስራት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ ማሽኖች መከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ድርጅቶች/ እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ።
1) ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የስራ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ።
2) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
3) የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑትን የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
4) በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5) የጨረታ ማስከበርያ ለሁሉም ሎቶቸ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በሌተር ኦፍ ክረዲት ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ።
6) የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
7) ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሰነድን ዋናውና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በሁለት ፖስታ ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በሸኮ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባችዋል።
8) ተጫራቾች ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
9) መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10) አቅራቢዎች የሚሞሉት ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት ካልሆነ መ/ቤቱ የተሞላውን ዋጋ ከነቫቱ እንደተሞላ አድርጎ ነው የሚወስደው
11) ይህ ጨረታ ለ60 /ስልሳ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ዕቃዎችን በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቀው እስከ ወረዳ ማእከል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
አድራሻ፡- ቤንች ሸኮ ዞን ሽኮ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0930573008
በ/ደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሽኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
