የደ/ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዘመን 2ኛ ዙር የጽህፈት መሣሪያ (Stationary) ግዥ በግል ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዘመን 2ኛ ዙር የጽህፈት መሣሪያ (Stationary) ግዥ በግል ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለዉ፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
3. PVAT /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ፤
4. የTin ተመዝጋቢ የሆነ፤
5. በ2018 ዓ.ም ግብር በመክፈል ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤
6. በOnline እቅራቢነት E-GP የተመዘገበና ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ
7. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትርበሥራ ሠዓት ለዶክሜንቱ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከእረካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት በሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን /Original/ በመያዝ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ላይ በማድረግ አንድ ኦርጅናሉን እና ሁለት የኦርጂናሉ ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግና ሙሉ አድራሻውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid security/ CPO 30,000.00/ ሰላሳ ሺህ ብር/ከታወቀ ባንከ በባንከ የተረጋገጠ /approved/ የተደረገ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በአረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር -8 ይከፈታል፡፡
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ተጫራቾች ያለመገኘታቸው የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር- 0913055185 ላይ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ
አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
