Tender Detail

Tender Details

  • Company የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም
  • Address ይ/ዓለም ከተማ : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-225-24-03
  • Website
  • Deadline28 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-28 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

በሲ/ብ/ክ/መንግሥት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ከሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለ6 (ስድስት) ተከታታይ ወር የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል እህል ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም


ለሕግ ታራሚዎች ቀለብ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ ቁጥር 03/2018

 

በሲ/ብ/ክ/መንግሥት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ከሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለ6 (ስድስት) ተከታታይ ወር የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል እህል ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

1

ነጭ መገኛ ሱፍ

በኩንታል

2

ቦቆሎ 1ኛ ደረጃ

በኩንታል

3

ባቄላ 1ኛ ደረጃ

በኩንታል

4

ፉርኖ ዱቄት 1ኛ ደረጃ

በኩንታል

 

ሕጋዊ ተወዳዳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ጨረታው የሚካሄድበት የሥራ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ሕጋዊ የጅምላ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን በ2018 ዓ.ም ያሳድሱ፡፡ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ የተጠቀሱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ ከይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋይን አስ የሥ/ ሂደት ክፍል ውስጥ ገዝተው ከሞሉ በኋላ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ አሥራ አምስተኛው ቀን 10፡20 ሰዓት ድረስ የታሸገውን ኤንቬሎፕ ወደ ጨረታ ሳጥን አስገብተው በዚህ ቀን በዕለቱ 10፡25 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ይከፈታል፡፡ የጨረታውን ሰነድ ለውድድር አቅርበው ከግል ፍላጎታቸው ሁኔታ የተነሳ በዕለቱ የማይገኙ ሲሆን የጨረታው ሰነድ ተከፍቶ ውጤቱ ይገለጽላቸዋል እንጂ የጨረታውን ሂደት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም፣ አንድ ተጫራች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ በጨረታ ሠነዱ የተመለከቱትን ዓይነቶች ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ ጊዜ ጀምሮ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አቅርበው ውል መፈጸም አለባቸው፡፡ አሸናፊዎችን አሸናፊነታቸው እንደተገለጸ ውል የማይፈጽሙ ሲሆን ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስም ይወረሳል)፡፡

የጨረታው ዝርዝር በጨረታው የአፈጻጸም መመሪያ ላይ የተገለጸ ስለሆነ በይበልጥ ተቀባይነት ያለው የጨረታ ሰነድ በመሆኑ አንድ በአንድ ማንበብ ይኖርባቸዋል፤ ጨረታ አውጪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-225-24-03 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም

ይ/ዓለም

Save Tender