Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
  • Address , Phone: 0118603257
  • Website
  • Deadline24 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-24 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ የመድኃኒት ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን


ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02 / 2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ የመድኃኒት ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ፎቶ ፣ ቪዲዮ ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የምትችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።

1-    ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣

2-    አነስተኛና ጥቃቅን ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3-    የመንግሥት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው

4-    ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5-    ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 401 ማግኘት ይችላሉ፡፡

6-    ተጫራቾች ማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ የመጫረቻ የጠቅላላ ዋጋ 2% CPO በማስያዝ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7-    ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8-    አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9-    አቅራቢዎች ቫትን ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አካተው ዋጋቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

10- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ስላሴ ቤተክርስቲያ ፊት ለፊት አምባሳደር ሞል ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ

ስልክ ቁጥር 0118 60 32 57

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ

መድኃኒት ባለስልጣን

Save Tender