Tender Detail

Tender Details

  • Company የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም
  • Address , Phone: 0465512117
  • Website
  • Deadline26 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price50.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-26 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ምግብ ዓይነቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም


ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ለ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት ከሚያዝያ ወር 2018 ዓም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ድረስ በሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት የህግ ታራሚዎች ምግብ ዓይነቶች፡-

ሀ. የሕግ ታራሚዎች መኖ እህል ዓይነቶች

ለ. የህግ ታራሚዎች መኖ ምግብ ማጣፈጫዎች

ሐ. የህፃናት አልሚ ምግቦች መ, አጥንት የሌለበት ቀይ የከብት ሥጋ/ቁም ከብት/ ለመግዛት በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎችን እና ከአደራጅ መ/ቤት የብቃት ማረጋገጫ ድጋፍ ያላቸውን የፋይናንስ ደንብና መመሪያ አሟልተው የሚቀርቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን ጨምሮ በማጫረት ከአሸናፊዎች ጋር ውል ተዋውሎ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ለአሸናፊው ግን ከውል ማስከበሪያ ዋስትና ጋር የሚታሰብ ለመኖ እህል ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ የህፃናት አልሚ ምግቦች ብር 20,000/ሀያ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከየጨረታው ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።

1.       ተጫራቾች ለሁሉም ጨረታዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በማይመለስ ብር 50/ሀምሳ/ ብር በመክፈል ከመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አነስቶ በተከታታይ ለ15 ሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት አለባቸው ።

2.       በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ10 ቀናት ውስጥ በአሸናፊው ዕቃ ዓይነት ባሸነፈው ዋጋ አስልቶ 10% ለማስያዣ ፈቃደኛ ካልሆነ እና አሸንፎም አላቀርብም ካለ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለመንግስት ውርስ ይደረጋል።

3.       ከላይ ከፊደል ተራ ሀ / እስከ ሐ/ ድረስ የተዘረዘሩ ዕቃዎች ዓይነት ፣ መለኪያና መጠን/ ብዛት ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በዝርዝር ተካቶ ይቀርባል።

4.       አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

5.       ተጫራቾች ለተዘረዘሩት ዕቃዎች በውድድሩ ቀን ናሙናውን ይዞ መቅረብ አለባቸዉ።

6.       ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውንና የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት እስከ ጨረታ ማብቂያ ቀን 7:30 ድረስ በጨረታው ሳጥን መጨመር ይኖርባቸዋል።

7.       ሁሉም ዕቃዎች ጨረታ ሳጥን ተዘግቶ የሚከፈተው በዕለቱ ከ7፡30 ሰዓት ድረስ በተቋሙ ቅጥር ግቢ በቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ተጨምሮ በ7፡35 ሰዓት ተዘግቶ ሁሉም ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል። ግን ዕለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

8.       የእህል ተጫራቾች ለመ/ቤታችን የዕቃዎች ማከማቻ መጋዘንና ቦታ ስለሌለው የቀጣዩን ወር በገባ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ተጠቃሎ ገቢ ሲያደርጉ የቀድሞ ወር ክፍያው ግን ወር በገባ እስከ 28ኛው ቀን ድረስ የሚፈጽም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

9.       አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ ዓይነት በራሳቸው ማጓጓዣ በማምጣት በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው።

10.   አሸናፊ አቅራቢዎች በዕቃዎች አቀራረብ ላይ የጥራትና የማስተጓጐል ችግር ቢፈጠር ለውል ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከመቀጣቱም በተጨማሪ ለተፈጠረው ችግር በሕግ ፊት ተጠያቂ ይሆናል።

11.   መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ/በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12.   ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 551 2117/ 09 16 10 75 78/ ይጠይቁን/

 

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም

Save Tender