በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ የቋሚ ቢሮ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ የህክምና እቃ እና የጥገና እና የፓርትሽን አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ የቋሚ ቢሮ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ የህክምና እቃ እና የጥገና እና የፓርትሽን አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፡-
1. የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡ ማስረጃ፣ ለጥገና እና ፓርትሽን ስራ ቢያንስ ደረጃ 6 የብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በሚገኘው ግዥ ከፍል አስተዳደር ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለየምድቡ (ሎት) የተመደበውን የብር መጠን በCPO ማስያዝ አለባቸው። ከአንድ በላይ በሆነ ሎት የሚሳተፉ ተጫራቾች ለየሎቱ የተመደበውን የብር መጠን ድምር በCPO ማስያዘ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነዶች እና የሞሉትን ዋጋ እና ኮፒ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ በወጣ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች ዋጋ ማቅረብ ያለባቸው ከጤና ጣቢያው በሚወስዱት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብቻ ነው፡፡
7. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስሙ ሰሜን ማዘጋጃ
ስልክ ቁጥር፡- 0111-12 94 72
በአራዳ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ
