Tender Detail

Tender Details

  • Deadline17 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price575.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-17 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ (ፑሚስ፣ ክሊንከር፣ ጂፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙለት የትራንስፖርት ድርጅቶችን በግልፅ የሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡


የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ

ቁጥር ሙሲፋ/2Re-58/2018

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ (ፑሚስ፣ ክሊንከር፣ ጂፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙለት የትራንስፖርት ድርጅቶችን በግልፅ የሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው (የ2018 ዓ/ም)፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (ከሆኑ) የታክስ ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የታክስ ክሊራንስ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምር በመከፈል የጨረታ ሰነዱ አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅደመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንት ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ደኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ ቁጥር፡- 0114420216

ፋክስ:- 0114420688

አዲስ አበባ

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

Save Tender