የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1090/2010 እና በሚኒስተሮች ደንብ ቁጥር 425/2010 መሰረት ያገለገሉ የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኢጽ/ግንአዳ/017/2018
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1090/2010 እና በሚኒስተሮች ደንብ ቁጥር 425/2010 መሰረት ያገለገሉ የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ከአካባቢ ደን የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለገሐር ከሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በመሙላት መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከ2፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ መነሻውን 20% (ሃያ በመቶ) ሲሆን ዝቅተኛው የማስያዣ ዋጋ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) በሚል ሥም የጨረታ ማስታወቂያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ለአንድ ዓይነት ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ ዕቃዎች መጫረት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሆኑበትን የዕቃ ዓይነት አጠቃላይ ዋጋውን በአስራ አምሰት ቀናት ውስጥ በመክፈል በአለበት ሁኔታ ተረክበው መውሰድ አለባቸው። ክፍያውን ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ።
8. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሆኑት ዕቃ ክፍያ የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ከሁለት ሳምንት በኋላ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
9. ጨረታው መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መሥሪያ ቤት ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
