የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/07/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
⁕ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
⁕ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት ለትሬዤሪ ክፍል ብሎክ አስራ አንድ G+2 የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈልና ደረሰኝ በመያዝ ሰነዱን ከትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
⁕ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/07/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
⁕ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የአቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
የታብሌት (Tablet) ግዥ |
ብር 517,500.00 |
የመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት |
የመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:05 ሰዓት |
⁕ ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
⁕ ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116732190 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
