የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል (Sidama National Regional State, Hawassa City Administration, Health Department, Hawela Tula General Hospital)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ኤሌክትሮኒክ 2. ደንብ ልብስ 3. ላቦራቶሪ ሪኤጀንት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
– ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ ጨረታ በሆስፒታሉ ስም ማሰራት አለበት፡፡
– የጨረታ ሰነድ በሰም ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ብሎ በፖስታ ላይ መጻፍ። ሲፒኦ ብቻ ያለበት በፖስታ ለብቻ መኖር አለበት። የጨረታ ሰነድ ተከታታይ (10) አስር የስራ ቀናት መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በ10ኛው ቀን ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6:00 ሰዓት በሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል በግዥና ክፍያ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
– ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
– መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0924302087/0916836497 ደውለው ይጠይቁ።
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል
