Tender Detail

Tender Details

  • Company ንብ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-40-16-50
  • Website
  • Deadline18 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-19 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Used Items , Vehicle

የንብ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ጐታች መኪናዎችና ተሣቢዎችን በውድቅዳቂ ብረታብረት እና ተሣቢዎችን፣ ወድቅዳቂ ብረታ ብረት (scrap) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ንብ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የንብ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ጐታች መኪናዎችና ተሣቢዎችን በውድቅዳቂ ብረታብረት እና ተሣቢዎችን፣ ወድቅዳቂ ብረታ ብረት (scrap) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1.     እያንዳንዱ ተጫራች ለ1ኪሎ ግራም ብረት የሚገዛበትን ዋጋ በዕቃው ዋጋ ማቅረብያ ሠነድ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ከየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት አሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት አስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ማስገባት ይችላል።

2.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ የጨረታ ሠነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡

3.     በአሸናፊ ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

4.     ተጫራች የጨረታ ሠነድ በሚያስገባበት ወቅት በባንክ የተረጋገጠ ሠነድ (cpo) ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል።

5.     የጨረታው ውጤት እንደታወቀ (cpo) ተመላሽ ይደረግለታል።

6.     ተጫራች ባሸነፈበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

7.     የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀናት ወስጥ የማንሣት ግዴታ የሚኖርብት ሲሆን ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ በመቀጫ ስም ለማህበሩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሠረዛል።

8.     የጨረታ ሳጥኑ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ/ም ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ ግቢ ወስጥ ይከፈታል።

9.     አክሲዮን ማህበሩ የተሻሉ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 011-4-40-16-50 ወይም 09-12-00-67-11/0913- 05-21-65 መጠቀም ይችላሉ።

 

ንብ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር

Save Tender