በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
1. የኤጀንሲው አድራሻ ፤ አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/ የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት/ ጨፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግሥት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -10፡30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6:30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
CPO ለማሠራት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-15-57-70-27
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
