Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: -046807970
  • Website
  • Deadline18 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-18 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል Walkthrough metal detector (የኤሌክትሮኒክስ መፈተሻ መሳሪያ) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል Walkthrough metal detector (የኤሌክትሮኒክስ መፈተሻ መሳሪያ) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡  ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

➢  የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

➢  የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈለና አግባብ ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

➢  በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማንኛውም ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ሙሉ መረጃ የያዘ ሰነድ ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡

➢  የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ.2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

➢  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው፤ ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድ እና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነዱን ለየብቻ በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጪ ገጽ ዋና/ኦርጅናል/ ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

➢  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን ሰነድ የሚያስገቡበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 5፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋው እና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ የተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል፡፡

➢  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ዋጋ 10,000.00 (አስር ሺህ) ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

➢  የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ እና ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046 807 970 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡

➢  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመ/ቤቱ አድራሻ፡- ወላይታ ሶዶ ከሌዊ ሪዞርት ፊት ለፊት

 

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

Save Tender